የዓለም ባንክ የሞጆ ደረቅ ወደብ ኮንቴይሮችን የማስተናገድ አቅምን በእጥፍ ለማሳደግ የሚያስችል የ150 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብድር መሥጠቱን አስታወቀ ።
የኢትዮጵያን 95 በመቶ የገቢ እቃዎችን የሚያስተናግደውና በአንድ ጊዜ 14ሺ 500 ኮንቴይነሮችን መያዝ የሚችለውን የሞጆ ደረቅ ወደብ አቅምን በሁለት እጥፍ ለማሳደግ የዓለም ባንክ 150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ብድር ሠጠ ።
የሞጆ ደረቅ ወደብ በ62 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝ ሲሆን በማስፋፊያ ሥራው በአጠቃላይ የደረቅ ወደቡ ስፋት ወደ 128 ሄክታር መሬት እንደሚያድግ ተገልጿል ።
በኢትዮጵያ የንግድ መርከብና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ የምህንድስና ኃላፊ አቶ አክሊለ ተሰማ ለፎርቹን እንደገለጹት ከዓለም ባንክ የተገኘው ብድር አገሪቷ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ የደረቅ ወደብን እንድትገነባ ያግዛል ።
ኢትዮጵያ የገቢ እቃዎችን ወደ አገር ውስጥ የምታስገባው በጅቡቲ ወደብ አማካኝነት ሲሆን የባቡር መሥመርን በመጠቀም የምታስገባውን ኮንቴይነሮች በሞጆ ደረቅ ወደብ ለማራገፍ እየሠራች ትገኛለች ።
የሞጆ ደረቅ ወደቡን ማስፋፋት ያስፈለገው በጅቡቲ ወደብ የሚከማቸውን ወደብ ጫና ለመቀነስ በማሰብ መሆኑን ተገልጿል ።
የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ካሮሊን ቱርክ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አሳካዋለሁ ለምትለው የኢንዱስትሪናየግብርና ዕድገት የደረቅ ወደብ አቅምን ማሳደግ እጅግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል ።
የደች ስቴደር ግሩፕ ሎጀስቲክስ ኩባንያ የሞጆ የደረቅ ወደብን ዚዳይን በማውጣትና የማስፋፋያ ግንባታውን ለማካሄድ የተመረጠ ሲሆን ኩባንያው ሁለት ተጨማሪ ደረቅ ወደቦችን ሃዋሳና በወረታ ከተማ ለመገንባትም እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ።