ማሻሻያዎች የተደረገበት የመአድን ስራዎች ደንብ በመአድን ማውጣት ወቅት የሚደርሰውን የአካባቢ መጎዳት ለመመለስ የሚያግዝ እንደሆነ የማእድን ፣ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የማእድን ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚንስትር ድኤታ አቶ ቴዎድሮስ ገብረግዛብሄር እንደገለጹት ፥ በተሻሻለው ደንብ ከትርፍ ለአካባቢ መልሶ ማልማት የሚከፈል ክፍያ የህግ ማእቀፍ እንዲኖረውም ተደርጓል።
ማሻሻያ የተደረገለት የመአድን ስራዎች ደንብ ፤ ከመአድን ማውጫ ፍቃድ አሰጣጥ እስከ መአድን አውጥቶ መአድን የወጣበትን አካባቢ እስከ ማልማት ሚደርሱ መሻሻያዎችን ያካተተ ነው ብለዋል።
እስካሁን ሲሰራበት የነበረው ድንብ እያንዳንዱ ስራ በህግ መሰረት አስገዳጅነት ኖሮት እንዲሄድ እና በስራው ሂደት ከፍተት ተፈጽሟል ሲባል ተጠያቂ እንዲሆን የሚያስችል አልነበረም።
እንደሚኒስትር ድኤታው ገለጻ ፥ይህም በተለይ ዘርፉ ላይ ችግሮች እንዲፈጠሩ ያደረገ መሆኑን እና ከችግሮቹ አንዱ በማአድን ማውጣት ወቅት የሚፈጠረው የአካባቢ ውድመት እንደ ማሳያ ነው።
የተሻሻለው ደንብ በተለይ ከፈቃድ አሰጣጥ እና አሰተደድር ላይ ቀልጠፋ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር ሊደረጉ እና ሊሟሉ ስለሚገባችው ነገሮች ይዘረዝራል።
በተለይም መአድን አካባቢዎችን መአድን ሲወጣባቸውም ሆነ ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ ሊደረግላቸው ስለሚገባ ጥንቃቄ ዝርዝር ጉዳዮቸን አስቀምጧል።
ሚንስትር ድኤታው አቶ ቴዎድሮስ ገብረግዛብሄር እንደሚሉት፤ ኩባንያዎቹ እንደሚያመርቱት ወይንም እንሚያወጡት የመአድን አይነት ከሚያተርፉት ትርፍ ለአካባቢው መልሶ ማልማት አንደሚያዋጡም ያስቀምጣል ።
ይህ ነጥብ አስገዳጅነት እንዲኖረው የተደረገውና ትርፍ ባያተርፉ እንኳን ከሰራ ማስኬጃ እንዲከፍሉ ግዴታ እንዲቀመጥ የተደረገው ፤ባለፉት ጊዜያት አልሚዎች ይህን ላለማድርግ የከስረናል ሀሰተኛ ማስረጃዎችን የማምጣት ልምድ እንዳላቸው አቶ ቴድሮስ ተናግረዋል ።
በመአድን ማልማት ስራ ላይ ብዙ ጊዜ ባለሃብቶች መአድን ለማልማት የያዙትን ሰፊ ቦታ ለብዙ ጊዜ በመያዝ ያቆያሉ።
ይህ ደግሞ ሌሎች አልሚዎች ወደዛ አካባቢ ገብተው እንዳይሰሩ ሲያደርግ መቆየቱ ለማወቅ ተችሏል።
ይህም በደንቡ መሰረት አልሚዎች በፍጥነት ወደ ስራ ገብተው በሚያስፈልጋቸው ቦታ ላይ ብቻ ስራ እንዲጀምሩ የሚያደርግ ነጥብንም አካቷል።
የተሻሻለው ደንብ በአሁኑ ወቅት የጸደቀ ሲሆን በአንድ ወር ህትመቱ ተጠናቆ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።
ይሀም በተለይ በመልሶ የአካባቢ ልማት ላይ ከአስገዳጅነት አንጻር የነበሩ ክፍተቶችን ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል-(ኤፍ ቢ ሲ)።