የኢትዮጵያን የቱሪዝም እምቅ አቅም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ 5ነጥብ5 ሚሊዮን ብር መመደቡን የኢትዮጵያ ቱሪዝም ደርጅት አስታወቀ ።
የድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጀማነህ ከድር እንደገለጹት ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ተደራሽነት ባላቸው መገናኛ ብዙሃን የማስተዋወቅ ሥራ ለማከናወን ነው የተመደበው በጀት የሚውለው ።
አዲሱን የቱሪዝም መለያ የአማርኛ አቻ ትርጓሜ "ምድረ-ቀደምት" ደግሞ ለአገር ውስጥ ቱሪስቶች እናስተዋውቃለን" ብለዋል።
ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም አቅም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብና ለአገር ውስጥ ጎብኚዎች የማስተዋወቁ ስራ በቀሪው ሩብ ዓመት እንደሚከናወንም ነው የተናገሩት።
የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላትም ቱሪዝሙን በማስተዋወቅ የአገሪቷን መልካም ገጽታ ለመገንባት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ይደረጋል ብለዋል አቶ ጀማል ።( ኢዜአ)