የቻይና የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራ ስኬታማ ሆኗል -አምባሳደር ላ ይፋን

ቻይና  ባለፉት  ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ   ተግባራዊ እያደረገች ያለችው የመሠረት ልማት  ግንባታ ኢንሽየቲቭ   ስኬታማ  ውጤት እያስመዘገበ  መሆኑን   በኢትዮጵያ   የቻይና ባለሙሉ ሥልጣን  አምባሳደር  ላ ይፋን ተናገሩ ።

በዛሬው ዕለት  በሂልተን   ሆቴል  በተካሄደው የአንድ ቀን  ፎረም ላይ የተገኙት  አምባሳደር  ሊ ይፋን  እንደገለጹት እኤአ  በ2013  በቻይናው ፕሬዚደንት ዢ ፒንግ  የተጀመረውና  ቻይናን ከመላው  ዓለም ጋር  በትብብር እንድትሰራ የሚያደርገው ኢኒሺየቲቭ   ዓላማው  እያሳካ ይገኛል ብለዋል ።

ኢንሺየቲቩ  ቻይና   ከተለያዩ  አገራት ጋር   በኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ የሁለትዮሽ ግንኙነትና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት   የተሻለ ውጤት  እንድታስመዘገብ  ትልቅ  እግዛ ማድረጉን  አምባሳደሩ ጠቁመዋል ።

ቻይና ኢትዮጵያን  ጨምሮ በአፍሪካ ውስጥ  የተለያዩ  የልማት ሥራዎች  በመሳተፍ  አፍሪካ  ከምዕራቡ ዓለም የሚደርስባትን  ተጽዕኖ  ሚዛናዊ  በማድረግ በኩል  የማይናቅ አስተዋጽኦ  እያደረገች  እንደምትገኝ  አምባሳደር ላ ይፋን አስረድተዋል ።   

እንደ አምባሳደሩ  ገለጻ ኢትዮጵያ  በኢኒሺየቲቩ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ  በመላው የአገሪቱ ክፍሎችን   በባቡር መሥመር  በማገናኘት  ጥረት ላይ ስትሆን  በቅርቡም የአዲስ አበባ  ጅቡቲ የባባር  መሥመር  ሥራውን  እንዲጀምር መደረጉ  የስኬታማ ውጤቱ አካል ነው  ።

በሚቀጥለው  የግንቦት ወር  ጠቅላይ ሚንስትር  ሃይለማርያም  ወደ  ቻይና ቤጂንግ  በማምራት   ቻይና  በመንገድ ዘርፍ በምታካሄደውን ጉባኤ ላይ    የመሠረተ  ልማት  ሥራው  ባስገኘችው  ውጤትና  በቀጣይ  የተሻለ ውጤት  ለማስመዝገብ  በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ  ተመልክቷል ።

ቻይና በኢትዮጵያ  ተግባራዊ   ያደረገቻቸው   ፕሮጀክቶች   በርካታ  ሥራ አጥ ኢትዮጵያውያንንም   ወደ ሥራ እንዲገቡ ያስቻሉ መሆናቸውን አምባሳደሩ ተናግረዋል ።