በያዝነው ክረምት 3ነጥብ5 ቢሊዮን ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ሚኒስቴሩ አስታወቀ
በመላ አገሪቱ ለሚካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 3ነጥብ5 ቢሊዮን ችግኞች መፍታላቸውን የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር አስታወቀ ።
የሚኒስቴሩ የደን ልማትና እንክብካቤ ዳይሮክቶሪየት ዳይሬክተር ወይዘሮ አብረኸት ገብረህይወት ለዋልታ እንደገለጹት፤ በያዝነው ክረምት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ህብረተሰቡን ባሳተፈ ሁኔታ ለሚካሄደው የችግኝ ተከላ ዘመቻ የሚውል 3ነጥብ5 ቢሊዮን ችግኞች ፈልተው ተዘጋጅተዋል ።
እንደ ወይዘሮ አብረኸት ገለጻ ለተከላ ዝግጁ ከሆኑት ችግኞች መካከል የተወሰኑት በበልግ ወቅት ዝናብ ባገኙ አካባቢዎች የተተከሉ መሆኑን ጠቅሰው ፤ክረምት ወቅት የሚተከሉ ።
ችግኞቹ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በሚገኝ ግማሽ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ የሚተከሉ መሆኑን አመልክተዋል ።
በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው የዝናብ እጥረት ምክንያት የችግኝ የማፍላትና የመትከል ሥራውን አስቸጋሪ ማድረጉን ወይዘሮ አብረኸት ጠቁመዋል ።
ህብረተሰቡ ችግኞችን ከተከለ በኋላ አስፈላጊው እንክብካቤ በማድረግ እንዲጸድቁ ማድረግ ይገባዋል ነው ያሉት ፡፡
ለዚሁም ህብረተሰቡ ችግኞችን በተገቢው መልሉ እንክብካቤ እንዲያደርግ የግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን በመጠቆም ።
የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በ2008 ዓም ሁለተኛ አጋማሽ በአገሪቱ የችግኝ መጽደቅ ደረጃ 67 በመቶ ተመዝግቧል ።
የአገሪቱ የደን ቆጠራ መረጃ እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በአሁኑ ወቅት 15ነጥብ5 በመቶ መሆኑ መድረሱ ነው የጠቀሱት ።