የ2011 ዓመት አጠቃላይ የኢፌዴሪ መንግሥት በጀት 346 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ሆኖ ፀደቀ

የኢፌዴሪ መንግሥት አጠቃላይ የ2011 ዓመት  በጀት 346 ነጥብ9  ሆኖ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው  ዕለት  ፀድቋል 

የህዝብ  ተወካዮች  ምክርቤት  በዛሬው  ዕለት  ባደረገው 5ኛው ልዩ  መደበኛ ስብሰባ  በ2011 ዓመት  ረቂቅ  በጀት  ላይ  ውይይት የተለያዩ  ጥያዌዎች  ለጠቅላይ  ሚንስትሩ  በማቅረብ  ምላሽ   ከተሠጠባቸው  በኋላ  በሙሉ  ድምጽ ፀድቋል 

ምክር ቤቱም ለዝርዝር እይታ ረቂቅ በጀቱን ለበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶ ውይይት ሲደረግበት የቆየ  ሲሆን ከ2010  ጋር ሲነጻጻር   የ 3ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ  ያለው  በጀት  እንዲጸድቅ  ተደርጓል ።

ከተመደበው  አጠቃላይ   የኢፌዴሪ መንግሥት  በጀት ውስጥ ለመደበኛ ወጪ 91 ቢሊየን 67 ሚሊየን 160 ሺህ 588 ብር እንዲሁም 113 ቢሊየን 635 ሚሊየን 559 ሺህ 980 ብር ደግሞ ለካፒታል ወጪ የተመደበ ነው።

በተጨማሪም  135 ቢሊየን 604 ሚሊየን 731 ሺህ 380 ብር የሚሆነው  ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ   የተመደበ ሲሆን  ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ደግሞ 6 ቢሊየን ብር ተመድቧል።

ጠቅላይ  ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ  የ2011 የበጀት  ድልድልና ሌሎች  ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊ  ጉዳዮችን በተመለከተ  ከምክር ቤቱ አባላት  ጋር  ለቀረበላቸው  ጥያቄዎች  ማብራሪያ  ምላሽ  ሠጥተዋል 

ጠቅላይ  ሚንስትር  ዶክተር አብይ የሚቀጥለው   የበጀት ዓመት   ድልድል  ለድህነት ቅነሳ  ላይ ትኩረት  በማድረግ  የተሠራ መሆኑን  አስተድተዋል 

ከአጠቃላይ   በጀቱ  64 በመቶ የሚሆነው   በአገሪቱ   ለሚገነቡና  ለሚካሄዱ   የመንገድ ፣ የመብራትና  የውሃ ፕሮጀክቶች  በመሳሰሉ የመሠረተ  ልማት  ፕሮጀክቶች  ላይ እንዲያተኩሩ    ተደርጓል  ብሏል ።

በበጀት ድልድሉ  ለክልሎች  አጠቃላይ  ሃብትን  በተገቢው መልኩ  የማዳረስ  ላይ የተኮረ  መሆኑንና የታዳጊ ክልሎችን የልማት ጥያቄን  ለመመለስና ችግሮችን  ለመፍታት  ትኩረት  አድርጎ የተመደበ መሆኑን  ጠቅላይ  ሚንስትሩ ተናግረዋል ።

ለ2011 ዓመት  የተመደበውን  በጀት  ለታለመለት  ዓለማ  መዋሉን   በጥብቅ  ቁጥጥርና ክትትል  የሚደረግና  እርምጃም  የሚወሰድ ስለመሆኑን  ጠቅላይ ሚንስትር  ዶክተር አብይ  አያይዘው  ገልጸዋል ።

የግል  ባለሃብቶች  ለአገሪቱ የኢኮኖሚ  ዕድገት በጎ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ መሆኑን የጠቆሙት    ጠቅላይ  ሚንስትሩ ባለሃብቶች ገንዘባቸውን ፣ እውቀታቸውንና ፈጠራቸውን ለማፍሰስ እንዲችሉ  ምቹ ሁኔታን መፍጠር  እንደሚያስፈልግ  ተናግረዋል ።

የአገሪቱን  የውጭ  ምንዛሪ  ግኝት  በአብዛኛው ከአነስተኛ ግብርና  ምርቶች የሚመነጭ  በመሆኑ  የግብርናውን ዘመናዊ በማድረግ የተሻለ ውጤት  በማስመዝገብ  የተሻለ የውጭ  ምንዛሪ  ለማግኘት  በትኩረት መሥራት  ይገባል ብለዋል ።

የውጭ ምንዛሪን  ክምችት ለማሳደግም   በዋነኝነት   ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ  ለመተካተ  ሊሠራ  እንደሚገባም  ጠቁመዋል      

ተለይ በማኑፋክቸሪንግ  ዘርፍ  የአገር ውስጥ  የሚያመርቱ  ባለሃብቶችን በመፍጠርና  ማገዝ  ያስፈልጋል ያሉት  ጠቅላይ ሚንስትሩ ለዘርፉ  የሚውለውን ግብዓቶች ወደ አገር ውስጥ  ለማስገባት  ከፍተኛ  የውጭ  ምንዛሪ እየወጣም  ይገኛል ብለዋል ።

የአገሪቱ  የማዕድን  ዘርፍ የተሻለ ገቢና ጥቅም እንዲያስገኝ ለማድረግ  በማዕድን በተገኙባቸው  አካባቢዎች የተሻለና በቀጥታ ተጠቃሚ  እንዲሆኑ  ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት  ጠቅላይ ሚንስትሩ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ   በሆነ ጊዜ   ሃብቱን  በአግባቡ  እንዲንከባከም  እግዛ ይኖረዋል  ብለዋል 

የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን  በተመለከተ  ጠቅላይ  ሚንስትሩ  ለምክር  ቤቱ  በሠጡት  ማብራሪያ   የፍላጎት ማደግና  የአቅርቦት  በበቂ ሁኔታ  ባለማደጉ  ምክንያት የሚከሰተ መሆኑን በመጠቆም   የነዳጅ  ዋጋ  በጨመረ  ቁጥር የሸቀጦች  ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ  እያደገ መጥቷል  ብለዋል ጠቅላይ ሚነስትሩ ።

የዋጋ  ግሽበቱን  ለመከላከልም ስንዴ ፣ ዘይት የመሳሰሉትን  ግብዓቶችን  በአገር ውስጥ  በበቂ ሁኔታ  ማምረት  እንደሚያስፈልግና በዋነኝነትም   የዜጎች ገቢ  በማሳደግም  የኑሮ ውድነትን ለመከላከል  መሥራትም እንደሚጠይቅ   ጠቅለይ  ሚንስትሩ  አመልክተዋል ።

የመንግሥትን   ገቢ  ለመጨመር   የገቢ  አሰባሰቡን  ዘመናዊ ማድረግ  እንደሚገባ  የገለጹት ጠቅላይ ሚነሰትሩ ባለሃብቶች  በግብር አሰባሰቡ  አስፈላጊውን  ትብብር  ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል 

በአገሪቱ  እየተከናወኑ ያሉት   ሜጋ ፕሮጀክቶች የመንግሥት  የልማት  ድርጅቶች በበላይነት የሚመሯቸው  መሆኑና  በግሉ ዘርፍ  ፈጽሞ የማይከናወኑ  በመሆኑ  ምን ያህል ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ  መሆኑን  በጥናት በማረጋገጥ   ፣ አፈጻጸማቸውነ በመገምገም  የተጀመሩ  ፕሮጀክቶች  በሙሉ አቅም  ተረባርቦ መጨረስ  አስፈላጊ መሆኑን   ለምክርቤቱ  አባላት  ጠቅላይ  ሚንስትሩ አስረድተዋል ።

ኢትዮጵያ  በአሁኑ ወቅት የጀመረቻቸውን ሜጋ ፕሮጀክቶች   ለማጠናቀቀም 7ነጥብ 5  ቢሊዮን እንደሚያስፈልጋት  ጠቅላይ  ሚንስትሩ አያይዘው ገልጸዋል 

ስለዚህም  በአሁኑ ወቅትም  አገሪቱ የጀመረቻቸውን ፕሮጀክቶችን  ሳትጨርስ  ሌላ አዲስ  ፕሮጀክቶችን  ብትጀምረ  ኢፍትሃዊ እንደሚሆንም  ተናግረዋል ።

የመንግሥት  የልማት ድርጅቶችም  ፕሮጀክቶችን ሃብት ለማስፈጸም  እስካሁን  ድረስ  400 ቢሊዮን  ያህል ብድር  ከአገር ውስጥ ባንኮች   መበደራቸውንና ፣ በፍጥነት  ሃብት ማፍራት ካልቻሉ  ለአጠቃላይ ኢኮኖሚውም  አደጋ  እንደሚሆኑ  አመልክተዋል ።

በመጨረሻም  ሁሉም  ሚነስትር መሥሪያ ቤቶች  በምክር ቤቱ  ቋሚ  ኮሚቴ  አስፈላጊው  ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ ኮንትራት   እንደሚፈራረምና  ተገቢው ውጤት  ያላስመዘገበ አመራር ላይ  እርምጃ  የሚወሰድበት አሠራር ይዘረጋል  ብለዋል ጠቅላይ ሚነስትሩ ።