የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ኤርትራ በረራ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ኤርትራ  በራራ  ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ ።

በረራው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ ባደረጉት ጉብኝት ሁለቱ ሃገራት የደረሱት ስምምነት አካል መሆኑ ተነግሯል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከጉብኝቱ በኋላ ለጋዜጠኞች በሠጡት መግለጫ ነው ይህን የገለፁት፡፡

በቀጣዩ ሳምንት በሚጀመረው የአውሮፕላን ጉዞ መንገደኞች መግቢያ ቪዛ የሚጠየቁ ሲሆን፥ በቀጣይ በሚኖረው ጉዞ ላይ መንገደኞች ያለ ቪዛ መግባት በሚችሉበት ሁኔታ ላይም ኮሚቴው እንደሚወያይ ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው በሁለቱ ሃገራት ጦርነት ወቅት የተያዙ የጦር ምርኮኞች እና እስረኞችን ጉዳይ በተመለከተም፥ ኮሚቴው ጥናት በማድረግ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚያቀርብም አንስተዋል።