8ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በሚመጣው ታህሳስ ወር በሶማሊያ ክልል ጂግጂጋ ከተማ እንደሚከበር ተገለጸ

8ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ከታህሳስ አንድ አስከ ሰባት 2011 ዓ.ም በሶማሊያ ክልል ጂግጂጋ ከተማ እንደሚከበር ተገልጸዋል፡፡

ለፎረሙ ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የተቀናጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ለከተሞች ልማት በሚል መሪ ቃል በሚከናወነው ፎረም ላይ ከ200 በላይ ከተሞች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በከተማ ልማትና ቤቶች ልማት የከተማ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ቢራሳ ተናግረዋል፡፤

በፎረሙ ላይ ከስምንት አስከ አስር ሺ ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ዝግጅቱን የሚያስተባብሩ፣ የከተሞችን እውቅናና ደረጃ የሚያወጡ ኮሚቴዎች ከወዲሁ እየተደራጁ መሆኑን ወይዘሮ ሂሩት ገልፀዋል፡፡

ፎረሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጅ እንደመሆኑ መጠን ከተሞች የኢንቨስትመንት ብሎም የቱሪዝም እድል ለማሰፋት ተሞክሮ የሚያሰፉበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡