ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ የ115 ሚሊዮን ፓውንድ የድጋፍ ስምምነት አደረጉ

ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ የ115 ሚሊዮን ፓውንድ የድጋፍ ስምምነት አድርገዋል፡፡

ድጋፉም ለኢንዱስትሪ ልማት እና የታክስ ስርዓትን ለማሻሻል በሚደረገው ሂዴት አጋዥ ይሆናል ተብሏል፡፡

የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም ተከስተ የተደረገው ድጋፍ ኢንግሊዝና ኢትዮጵያ ያላቸው የቆየ ትብብር ጥሩ ደረጃ ላይ እንዳለ የሚያሳይ የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ በተጨማሪም ድጋፉ በኢንዱስትራላይዘሽን ስራ ላይ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ከ30ሺህ በላይ ስደተኞች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ኃላፊዋ ፔኒ ሞርዳንት በበኩላቸው ለኢንዱስትሪ ልማትና ስራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም የኢትዮጵያን የታክስ ስርዓት ለማሻሻል የተደረገው ድጋፍ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ያደርሰዋል ብለዋል፡፡

በቀጣይም ነትምህርት፣ በጤና፣ በመሰረተ ልማት እና ሌሎች ዘርፎችም ለኢትዮጵያ የሚደረገው ድጋፍ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡