ባለቤት የሌላቸውን ሕንፃዎችና ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችን ማግኘቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ

የአዲሰ አባበ ከተማ አስተዳደር  እያካሄደ ባለው የማጣራት ሥራ ባለቤት የሌላቸውን ሕንፃዎችና ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችን ማገኘቱን አስታውቋል።
ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እንደገለጹት አዲሱ አመራር ሃላፊነት በተረከበ  ማግስት የማጣራት ስራውን ለመስራት  10 ቡድኖችን በማደራጀት በሁሉም ክ/ከተሞች ማሰማራቱን ጠቁመዋል፡፡

 በአንድ ወር ውስጥ በተገኘው መረጃ ብዙ የተሰሩ ህንፃዎች እና የታጠሩ ቦታዎች ባለቤት የላቸውም ያሉት ምክትል ከንቲባው ብዙ ኮንዶሚኒየም ቤቶች በግለሰብ ተይዘው እንደሚገኙና ይሄንን አጥርተው ለህዝብ በዝርዝር ይፋ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡

ኢንጂነር ታከለ አያይዘውም ብዙ ሃብት እያላቸው የቀበሌ ቤት እና ኮንዶሚኒየም ይዘው የድሃውን ሃብት የሚሻሙ ብዙ ናቸው ያሉ ሲሆን ይሄንን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲፋረዳቸው እናደርጋለን በማለት ተናግረዋል፡፡ ለጊዜው እንዲቆም የተደረገው የመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮችም መስከረም ላይ ይጀምራል ብለዋል፡፡

እስከ ፊታችን አዲስ ዓመት ድረስ የማጣራት ሥራው ተጠናቅቆ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አመልክተዋል።