ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ከቻይና ባለሀብቶች ጋር ተወያዩ

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በቻይና ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሳን ሩዢ ከሚመራው የቻይና ባለሃብቶች ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውውይቱ ወቅትም ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ፥ በኢትዮጵያ ለጨርቃ ጨርቅ አልባሳት ዘርፍ መንግሥት የሚሰጣቸውን ድጋፎች ምቹ ሁኔታዎች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የቻይና ባለሀብቶችም በበኩላቸው በኢትዮጵያ ያለው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታና እምቅ አቅም በዘርፉ ለመሰማራት እንዳነሳሳቸው ገልጸው፣ የፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ማብራሪያም እንዳስደሰታቸውና በቀጣይም በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ባለሐብቶቹ የሐዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡

የቻይና ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ብሔራዊ ምክር ቤት በቻይና ጨርቃ ጨርቅና ተያያዥ ኢንዱስትሪ ዘርፎች የተሰማሩ ከ3 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞችና የጨርቃ ጨርቅ ማህበራትን ያቀፈ ነው።