የአፍሪካ የጥጥ፣ ጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት አውደ ርዕይ ዛሬ ተከፈተ

የአፍሪካ የጥጥ ፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት አውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ተከፈተ ።

በአውደ ርዕዩም  ላይ ዘመናዊ የቤት ውስጥ ንድፎችን አልያም ኢትሪየር ዲዛይን ለእይታ ቀርበዋል፡፡  አውደ ርዕዩ እስከ ሀሙስ ለህዝብ ክፍት ሆን እንደሚቆይ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሚካሄደው አውደርዕይ በጥጥ ጨርቃ ጨርቅ የተስሩ አልባሳት፣ የቆዳ ውጤቶች፣ ከዘርፉ ጋር የተያያዙ የቴክኖሎጂ  ወጤቶች እና ቤት በንድፍ በማስዋብ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንደስትሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ከ250 የሚበልጡ ዓለም አቀፍ አምራቾች እና ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ተቋማት ምርቶቻቸውንና አዳዲስ ፈጠራዎቻቸውን ከ4ሺህ ለሚበልጡ ተቋማት ያስተዋውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከመላው ዓለም የተውጣጡ ነጋዴዎች እና ገቤያ አፈላላጊዎች ምርታቸውን እና አገልግሎታቸውን ለዕይታ ያቀርባሉ ተብሏል፡፡

በዚህኛው አውደ ርዕይ ለመጀመሪያ ጊዜም ከ12 የሚበልጡ የደቡብ አፍሪካ የቆዳ ውጤቶች አምራቾች ተሳትፈዋል፡፡

ኩባንያዎቹ ክህሎታቸውን እና ምርቶቻቸውን ለዓለም አቀፍ ፋሽን አቅራቢዎች እና ሸማቾች ለማስተዋውቅ እና ለመሽጥ አቅደዋል፡፡  

የኢትዮጵያ፣ ግብፅ ፣ቻይና እና ፓኪስታን ኢንደስትሪዎችም እየተሳተፉ  ሲሆን በእንዲህ አይነት አውደ ርዕይ መሳተፍ የንግድ ትስስርን ከመፍጠር አንጻር ጠቀሜታው የጎላ ነው መሆኑን  ለዋልታ  ተናግረዋል ፡፡

የቆዳ ውጤቶችን ይዛ የቀረበችው ዲዛይነር ሰናይ እንደምትናገረው  ከዚህ ቀደም ካሉት ጊዜያት ጋር ሲነጻጸር የቆዳ ምርቶች ላይ የተሻለ ለውጥ እንዳለ በመጠቆም  አልፎ አልፎ በሚፈጠር የቆዳ ጥራት ችግር ግን በዘርፉ  በተሠማሩ  ግለሰቦችም አሁንም ለኪሳራ ይዳረጋሉ  ብላለች፡፡

በአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት አውደዕርይ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንደስትሪ ልማት ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ስለሺ ለማ  አውደ ርዕዩ የውጭ ባለሃብቶችን ከመሳብ አንጻር ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በተጨማሪም በዘርፉ የተሠማሩ የሀገር ውስጥ አምራቾችና አቅራቢዎች ጥራት ያለው ምርትን ወደ ውጭ  በመላክ ረገድ ችግር እንዳለ አንስተዋል፡፡