በኮፐንሀገን ሲካሄድ የቆየው ለአረንጓዴ ልማትና ለዘላቂ ልማት ግቦች አለም አቀፍ ትብብር ጉባኤ ተጠናቀቀ

በኮፐንሀገን ዴንማርክ ሲካሄድ የቆየው ለአረንጓዴ ልማትና ለዘላቂ ልማት ግቦች አለም አቀፍ ትብብር ጉባኤ ተጠናቀቀ።

በጉባኤው ላይ ተሳታፊ የነበሩት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፥ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የምትሰጠውን ትኩረት አስመልክተው ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከጉባኤው ጎን ለጎንም ከዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሎክ ራስሙሰን ጋር፥ በሁለቱ ሀገራት የልማት ትብብር እና የአጋርነት መስኮች ላይ ተወያይተዋል።

በተጨማሪም በሎጅስቲክስ አቅርቦት ከሚታወቀው ማረስክ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ሶረን ሶኩ ጋር መወያየታቸውም ይታወሳል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ያለውን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጭ ለመመልከት በሚቀጥለው ወር ተወካዮቹን ወደ አዲስ አበባ እንደሚልክም አስታውቋል።

በጉባኤው ላይ የአየር ንብረት ለውጥ በመከላከል ረገድ መልካም ተሞክሮ ያሳዩ ተቋማት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።(ምንጭ:ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት )