የ2010/2011 የክረምትና የበልግ የአየር ሁኔታ ለሰብል አመቺ መሆኑን ቢሮው አስታወቀ

የ2010/2011 የክረምት እና የበልግ የአየር ሁኔታ ለሰብል አመቺ ሆኗል ሲል የኦሮሚያ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ገለፀ፡፡

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በተወሰኑ አካባቢዎች ዝናብ ዘግይቶ ገብቶ ዘግይቶ ቢወጣም በአብዛኛው የክልሉ ቦታዎች ግን የአየር ሁኔታው ጥሩ ምርት እንዲሰበሰብ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ 4ነጥብ 5 ሚልዮን ሄክታር መሬት ላይ የበቀለው አረም በህብረተሰቡ አማካኝነት እንደተወገደ የተናገሩት የቢሮ ኃላፊው አቶ ዳባ ደበሌ አሜሪካ መጣሽ ተምች ከ343 ሺህ ሄክታር በላይ በላው ሰብል ላይ ተከስቶ ጉዳት ሳያደርስ በባህላዊ እና በኬሚካል አማካኝነት መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል፡፡

የሚሰበሰበው ምርት እንዳይቀንስ እና ጥራቱንም እንዳያጣ በተደራጀ መልኩ በባለሙያዎች ድጋፍ ጭምር ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡