በደቡብ ክልል 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ስራ ላይ ያልዋለ በጀት መኖሩ ተረጋገጠ

በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች  ክልል  3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ስራ ላይ ያልዋለ በጀት መኖሩ ተረጋግጧል፡፡

በክልሉ በ133 መስሪያ ቤቶች በወቅቱ መወራረድ ሲገባው ያልተወራረደ 629 ሚሊዮን 982 ሺ ብር መኖሩ ታውቋል፡፡

በ137 መስሪያ ቤቶች 128 ሚሊዮን ብር ማስረጃ ሳይቀርብ፣ የተሟላ ማስረጃ ሳይኖርና ህጋዊ ባልሆነ ማስረጃ ተወራርዶ እንዲሁም ተመዝግቦ ተገኝቷል፡:

በስድስት መስሪያ ቤቶች ረጅም ጊዜ ያስቆጠረና ከማን እንደሚሰበሰብ የማይታወቅ 54 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር እንዳለ ተረጋግጧል፡፡

በ42 መስሪያ ቤቶች 32 ሚሊዮን 19 ሺ ብር ማስረጃ ሳይኖረው የተመዘገበና ማስረጃው ለኦዲት ባለመቅረቡ ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ ያልተቸለ የወጪ ሂሳብ መኖሩ ተመልክቷል፡፡

18 ሚሊዮን 664 ሺ ብር ከደመወዝ ያልተቀነሰ ግብር እንዳለ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

43 መስሪያ ቤቶች ሕጉን በመጣስ ከፍተኛ ዋጋ ካቀረቡት መስሪያ ቤቶች የ15 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ግዥ ፈጽመዋል፡፡

144 መስሪያ ቤቶች 14 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ያለአግባብ አበል ከፍለዋል፡፡

በ 67 መስሪያ ቤቶች በ13 ሚሊዮን 75 ሺ ብር ተገዙ ለተባሉ እቃዎች የንብረት ገቢ ማስረጃ ሊቀርብ አለመቻሉ ተደርሶበታል፡፡/ዘገባው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነው/