በአዳማ ከተማ 10ሺህ 200 የአሜሪካን ዶላር በቁጥጥር ሥር ዋለ

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 10ሺህ 200 የአሜሪካን ዶላር በአዳማ ከተማ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ መመምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ሳጅን ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለጹት ዶላሩ በህገወጥ መንገድ በግለሰቦች ሲዘዋወር ትናንት ማታ 3፡30 ላይ ህብረተሰቡ ባደረገው ጥቆማ ሊያዝ ችሏል።

ገንዘቡ የሰሌዳ ቁጥሩ 2-17781 (አ.አ) በሆነ የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪ ተጭኖ ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በፍጥነት በመጓዝ ላይ እያለ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ልዩ ስሙ "ናማልድ" በተባለ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ከመኪናው ጋር በተያዙ ሁለት ግለሰቦች ላይ በፖሊስ በኩል ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ሳጅን ወርቅነሽ አመልክተዋል።

ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩን በተቀናጀ መልኩ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ትብብር በቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።(ኢዜአ)