ድርጅቱ ከቤኒዝን ጋር በተያያዘ የተከሰተውን ችግር ለመፍታት እንቅስቃሴዎች መጀመሩን አስታወቀ

በአዲስ  አበባ ከተማ  የተፈጠረውን የቤንዚን እጥረት ችግር ለመፍታት እንቅስቃሴዎች  መጀመሩን  የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ ።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለማሪያም በዛሬው ዕለት በሠጡት መግለጫ እንደገለጹት  ከቅርብ  ጊዜ  ወዲህ  በአዲስ አበባ ከተማ  የተከሰተው የቤንዚን  እጥረት ችግር  ከአቅርቦት  ጋር በተያያዘ  ሳይሆን  በአገር ውስጥ  ህገ ወጥ  የነዳጅ  ንግድ ምክንያት መሆኑን አስረተድተዋል ።

እንደ አቶ ታደሰ ገለጻ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በነዳጅ ኮንትሮባንድ ንግድ  አማካኝነት ቤኒዝን  ወደ  ጎረቤት  አገራት በበርሜል  ተጓጉዞ  እየተሸጠ  በመሆኑ  የቤኒዝን  እጥረት ተከስቷል ብለዋል ።

በአጠቃላይ  ከቤኒዚን ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን  ችግር  ለመቅረፍም ድርጅቱ   የተለያዩ  እርምጃዎችን  መውሰድ መጀመሩንም  አቶ  ታደሰ  በመግለጫቸው ተናግረዋል ።

በአገሪቱ  እየታየ ባለው ህገ ወጥ  የነዳጅ  ንግድ እየተሳተፉ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችም  ከእንደዚህ አይነት ድርጊት  እንዲቆጠቡም  አቶ ታደሰ  ጥሪ አቀርበዋል ።

ህብረተሰቡም  ህገ ወጥ የነዳጅ  ንግድ ላይ  የሚሳተፉ አካላትን ህገወጥ ድርጊት ሲፈጽሙ  በሚያይበት  ወቅት  ለሚመለከታቸው አካላት  ጥቆማውን  እንዲሠጥም  ጥሪ አስተላልፈዋል ።

በኢትዮጵያ  የነዳጅ  የችርቻሮ ዋጋ  ከጎረቤት አገራት ጋር ሲነጻጻር  አነስተኛ  መሆኑ  ይገለጻል ።

የኢትዮጵያ  ዓመታዊ   የነዳጅ  ፍጆታ  በ10 በመቶ  የሚያድግ  ሲሆን   አጠቃላይ  የነዳጅ  ግዥ ወጪው   3  ቢሊዮን  ዶላር ደርሷል  ።