አዉሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ 20 ሚሊየን ዩሮ የእርዳታ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ 20 ሚሊዮን ዩሮ የእርዳታ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ ።

ስምምነቱ የተደረገዉ በኢፌዴሪ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ የአዉሮፓ ህብረት የልዑካን ቡድን መሪ ኢሪክ ሀብርስ መካከል ተፈራርመዋል፡፡

ከህብረቱ  የተገኘው  ድጋፍ በዋናነት የሴቶችንና ህፃናነትን አመጋገብ እና ጤና ለማሻሻል የሚውል ሲሆን መንግስት የሚያድረገውን አካታች ዕድገትና ድህንነትን ለመቀነስ የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ ይሆናል፡፡

ድጋፉ የሚውለው በአፋር፣ቤንሻንጉል ጉሙዝና ጋምቤላ ክልሎች የሚሰጠውን የጤና አግልግሎት ተደራሽነትና ጥራት ለማሳደግ እንዲሁም አንዳንድ ጎጂ ልማዶችን ለመቀነስ የሚውል ይሆናል ብለዋል፡፡

ህብረቱ እና የህብረቱ አባል ሃገራትም ዲፕሮማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርም ከንግድ እና የእርዳታ ድጋፍ የሚሻገር መሆኑን በኢፌዴሪ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አድማሱ ነበበ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአዉሮፓ ህብረት ትብብር መሪዉ እንደተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ ለሚመራዉ መንግስት ፅኑ ድጋፍ መኖሩንና ህብረቱም ሆነ አባል ሃገራቱ በመሠረተ ልማት እና በሌሎች የድጋፍ ስራዎች ለመሥራት ፋላጎት ማሳያ ነዉ ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ዉስጥ እየስተዋለ ያለዉ ሀገራዊ ለዉጥ የአዉሮፓ ህብረት አባል የሃገራቱን አወንታዊ ትኩረት እየሳበ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡