ኢትዮጵያ የመስመር ላይ የኢንቨስትመንት መመሪያ ይፋ አደረገች

ኢትዮጵያ እኤአ ከዴሴምበር 21፤2018 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ በድህረ ገፅ የተደገፈ አዲስ የመስመር ላይ የኢንቨስትመንት መመሪያ ይፋ አደረገች።

መመሪያው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና በተመድ የንግድ ልማት ኮንፈረንስ ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን ዓላማውም ውጤታማ ኢንቨስተሮችን ወደ አገሪቱ ለመሳብ እንደሆነ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ከማዳጋስከርና ሞሪሸስ በመቀጠል የመስመር ላይ የኢንቨስትመንት መመሪያ ይፋ ያደረገች ሰባተኛዋ የአፍሪካ አገር መሆኗ ተገልጿል፡፡ (ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት)