በተለያዩ ዘርፎች እየታየ ያለው ለውጥ ወደ ኢኮኖሚክ ሪፎርም ማደግ እንዳለበት ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባዘጋጀው የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ዘርፎች እየታየ ያለው ለውጥ ወደ ኢኮኖሚክ ሪፎርም ማደግ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

በዚሁም እያንዳንዱን ነዋሪ በቀጥታ ተጠቃሚ ሊያደርግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

አመራሩም ይሄን በመገንዘብ በተለይም የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመቅረፍ ነዋሪውን ማርካት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ ትራንስፖርት፣ ውሀ እና ቤቶች ዘርፍ ላይ ከምንም በላይ ቅድሚያ ሰጥቶ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ እና በሂደቱም ወጣቶች በስፋት የስራ እድል የሚያገኙበት አና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር እንደሚከተል አንስተዋል።

አሁን በከተማዋ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ከዳር እንዲደርሱ አመራሩ በቅድሚያ ለውጡን መቀበል እንዳለበት የጠቆሙት ምክትል ከኒቲባው አስተዳደሩ ባለፉት ወራት ህግን ለማስከበር እና ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ የጀመራቸው ስራዎች አሁንም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። (ምንጭ፡-የከንቲባ ጽህፈት ቤት)