ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከዱባይ ኢንቨስትመንት ፈንድ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ መሀመድ አል ሼይባን ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከዱባይ ኢንቨስትመንት ፈንድ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ መሀመድ አል ሼይባን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒትር ዶክተር አብይ ከኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መሀመድ አል ሼይባን ጋር የተወያዩት በዳቮስ የአለም ኢኮኖሚ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው፡፡

የዱባይ ኢንቨስትመንት ፈንድ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ በመስተንግዶና በእርሻ ቢዝነስ መዋእለ ንዋይ ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው የኮርፖሬሽኑ ስራአስፈፃሚ መሀመድ አልሸይባን ገልጸዋል፡፡ (ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)