የታላቁ ህዳሴ ግድብ 8ተኛ አመት የህዝብን ጥርጣሬ በሚያስወግድ መልኩ ይከበራል

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተጀመረበትን 8ተኛ አመት በተለያዩ ፕሮግራሞች መጋቢት 24 ቀን እንደሚያከብር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የጸ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀይሉ አብራሀም ለዋልታ እንደተናገሩት በአሉ ህዝቡ በግድቡ ላይ የነበረዉን የእምነት መሸርሸር በሚመልስ መልኩ ይከበራል ብለዉል፡፡

ህዝቡ በግንባታዉ ዙሪያ ብዙ ጥያቄ ያነሳ እንደነበረ ያነሱት አቶ አብራሀም  በአሉ ብሄራዊ መግባባትንና መንግስት እየወሰደ ያለዉን እርምጃ ለህዝብ ለማስረዳትም ይጠቅማል ብለዉል፡፡

አቶ ኃይሉ ከቦንድ ግዥ ጋር ተያይዞ የተነሳዉ የህዝብ ጥያቄም መፈታቱን ተናግረዋል፡፡

ብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሲሰራዉ የነበረዉ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ በሌላ ድርጅት በመያዙ ስራዉ ጥሩ እየሄደ ነዉ ብለዋል፡፡