የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የተሰራው ስራ ውጤታማ እንደነበር ተገለጸ

ባለፉት ስድስት ወራት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የተሰራው ስራ ውጤታማ እንደነበር የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መኮንን እንደገለጹት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የማስተዋወቅ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

እንደ አቶ መኮንን ገለጻ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ለ1 ሺህ 882 የውጭ ባለሃብቶች በሃገሪቱ ስለሚገኙ የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ገለጻ ተደርጓል፡፡

በዚህም የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን የእቅድ አፈጻጸሙም 164 በመቶ እንደሆነ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መዳረሻነቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን አቶ መኮንን ገልጸው የውጭ ባለሃብቶችም በሃገሪቱ ላይ ያላቸው አመኔታ እያደገ ይገኛል ብለዋል፡፡