የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ በአንድነት መንፈስ መሰራት እንዳለበት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ በአንድነት መንፈስ መሰራት እንዳለበት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ከዚህ በፊት የነበረው ህዝባዊ መነሳሳት እንዲቀጥልና መንግስት በግድቡ ዙሪያ የሚከናወኑ ስራዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ማድረስ እንዳለበትም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡

ግድቡም ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥና በህብረተሰቡ ዘንድ አመኔታ አንዲኖር መንግስት በትኩረት እየሰራ አንደሆነ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም ገልጸዋል፡፡

ከቦንድ አከፋፈል ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን ጥናት በማድረግ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ግድቡ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተጠናቆ ኃይል ማመንጨት ባይችልም የግንባታ ስራው አሁን ላይ 65 በመቶ መድረሱ ተገልጿል፡፡

በቅርቡ የግንባታውን ስራ ለማስቀጠል ከግንባታ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት 8ኛ ዓመት በዓል የፊታችን መጋቢት 24 በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡