ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከቻይና ሬልዌይ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የቻይና ሬልዌይ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ኢትዩጵያና ጂቡቲን የሚያገናኘዉን የባቡር ፕሮጀክት ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ ተገልጿል::

በቀጣይነትም የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስቱሪ ፓርክ ግንባታና የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎታቸዉን አሳይተዋል::

እንዲሁም የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት ላይ እንደሚካፈሉ ማሳወቃቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::