የኢንቨስትመንት ዘርፉ የሚጠበቅበትን ያህል ጥቅም እንዳይሰጥ የመንግስት መዋቅሮችና ተቋማት ክፍተት አለባቸው ተባለ

የኢንቨስትመንት ዘርፉ የሚጠበቅበትን ያህል ለሀገር ጥቅም እንዳይሰጥ የመንግስት መዋቅሮች እና ተቋማት ክፍተት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ኢንቨስትንት ኮሚሽን በከተማዋ እና ዙሪያ ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር በዘርፉ በሚታዩ ችግሮች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡

በዘርፉ የታዩና በኮሚሽኑ ጥናት የተለዩ ተግዳሮቶች የተመላቱ ሲሆን፣ በዚህም የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት በተናጠል መጓዝ፣ መንግስት ለዘርፉ አስፈላጊዉን የሙያና ቴክኒክ ድጋፍ አለማድረግ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታና አቅርቦት ማነስ እና ተያያዥ ጉዳዮች እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የመድረኩ ተሳታፊ የነበሩ ባለሀብቶች እንደገለፁት በተለይም ለሀገር በቀል ባለሀብት የሚሰጠው ግምት አነስተኛ መሆኑ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈጠረው አለመረጋጋቶች፣ ለሀገር በቀል ባለሀብቶች ብቻ የተፈቀዱ ምርቶች በውጭ ባለህበቶች ጭምር መመረታቸው እና ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ መበራከት ሌላኛው ችግር ነው ተብሏል፡፡

በዘርፉ የተስተዋሉ ችግች ዘርፉን ከማቀጨጩም ባሻገር ባላሀብቱን ለምሬት ዳርገዋል ያለው የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡

በኢድስ አበባና ዙሪያዋ በኢንቨስትንመንት ፍቃድ ወስደው የተመዘገቡት ባለሀብቶች ከ40 በላይ እንደሚሆኑ የገለፀው ኮሚሽኑ ከእነዚህ የሚገኘው ጥቅም አነስተኛ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ችግሮቹ መኖራቸው የሚታመን ነው ያለው የከተማዋ ኢንቨስተምንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አብዱልፈታህ ዩሱፍ ችግሩን ለመፍታት የመፍትሄ እርምጃዎችን እንደሚወስድ እና ፈጣን ለውጥን እንደሚያመጣ አስታውቀዋል፡፡

ይህ እንዲሳካ ግን ባለሀብቱን ጨምሮ የሚመለከታቸው ተቋማት በጋራ ለመስራት መዘጋጀት አለበቸው ብሏል፡፡

የተነሱት ጥያቄዎች የፖሊሲ ለውጥ የሚሹ ሳይሆኑ በትግበራ ወቅት ያጋጠሙ ናቸው ያሉት ኮሚሽነሩ ጥያቄዎቹን ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንሰራለን ብለዋል፡፡