ኮሚሽኑ የአስር አመት የልማት እቅድ እያዘጋጀ መሆኑን ገለፀ

የፕላንና ልማት ኮሚሽን የመጭዉን አስር አመት የልማት እቅድ እያዘጋጀ መሆኑን ገለፀ፡፡

ኮሚሽኑ ይህን የገለፀዉ ከመጋቢት እስከ መጋቢት ያከናወናቸዉን ተግባራት ዛሬ ለመገናኛ ብሁሃን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነዉ፡፡

የህዝብ ቆጠራ አለመካሄዱ ተፅዕኖ ቢኖረዉም በባላፈዉ ግምት እቅዱን ማዘጋጀት እንደሚቻል የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር  ፍፁም አሰፋ ገልፀዋል፡፡

እንደ ኮሚሽነሯ ገለፃ “ሀገራዊ የአስር አመት መሪ የልማት ፕላን ዝግጅት፣ ሀገራዊ የልማት እቅድ አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ስርአት ማዘጋጀት እንዲሁም የልማት ፕሮጀክቶች አመራርና አስተዳደር የህግ ማእቀፍ ዝግጅት” ኮሚሽኑ ያከናወናቸዉ ዋና ዋና ተግባራት ናቸዉ፡፡

የትልልቅ ፕሮጀክቶች መጓተት ደግሞ ክፍተት ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን ዶክተር ፍፁም ጨምርዉ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሯ  ችግሮችን ለመፍታትና በቀጣይ ስራዎችን ለማቀላጠፍ  ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች ጋር በመሆን ጥናት ተጠናቋል ብለዋል፡፡