ማቱክ የቡና አምራችና አቀነባባሪ ፋብሪካ በኢትዮጵያ የምርት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባለሃብቶች የሚተዳደረው ማቱክ የቡና አምራችና አቀነባባሪ ፋብሪካ በኢትዮጵያ የምርት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገለጿል፡፡

በተጨማሪም ፋብሪካው በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ተሰማርቶ ቡናን የማምረት ፍላጎት እንዳለውም አስተውቋል፡፡

ፋብሪካው ባለፉት 50 ዓመታት በላይ በቡና ምርትና ማቀነባበር ዘርፍ ቡናን በተለያዩ ውጤቶች በማምረት ለዓለም ገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡

ከዚህ ቀደም የሚረከባቸው የኢትዮጵያ ቡናዎች በተለያዩ ሃገራ ዳግም ለውጭ ገበያ የቀረቡ ሲሆኑ አሁን በቀጥታ ምርት ተጠቃሚ ለመሆን በመቻሉ እድለኛ እንደሆነ የፋብሪካው ባለቤት ሰሚራ ማቱክ ገልጸዋል፡፡

እንደ እሳቸው ገለጻም በቀጣዩ ወር አጋማሽ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አስፈላጊውን ጥናት እንደሚያደርጉ ተናረዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለዚህ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለጹት ደግሞ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ከፌደራል እስከ ክልል ያሉ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ለውጭ አምራቾች ምቹ ሁኔታን መፍጠር አለባቸው ብለዋል፡፡

በሁለቱ ሃገራት መካከል በተፈጠረው ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በርካታ ባለሃቶች ወደ ኢትዮጵያ ለመግባ ፍላጎት እያሳዩ መሆናቸውን አምባሳደር ሱሌይማን ጠቁመዋል፡፡