የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 2 ፕሮጀክቶች 800 ሚሊየን ዶላር በጀት አጸደቀ

የዓለም ባንክ ቦርድ በኢትዮጵያ ለሚተገበሩ 2 ፕሮጀክቶች የሚውል ተጨማሪ 800 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በጀት ማጽደቁን አስታወቀ፡፡

ከጸደቀው በጀት ውስጥ 500 ሚሊዮን ዶላሩ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ዘላቂ ልማት ለማምጣት የሚውል ሲሆን 300 ሚሊዮን ዶላሩ ለመጠጥ ውሃና ፍሳሽ ፕሮጀክቶች እንደሚውል ታውቋል::

ባንኩ ከ3 ሳምንት በፊት 350 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የአርብቶ አደሩን ህይወት ለማሻሻል እና 200 ሚሊዮን ዶላር ለኢንቨስትመንት ዋስትና ማጽደቁ ይታወሳል፡፡

በዓለም ባንክ ታሪክ በዚህ መጠንና ፍጥነት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ተደርጎ እንደማያውቅ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ገልፀዋል፡፡

ድጋፉ በአገሪቱ ያለው ለውጥ ምን ያህል ተስፋ ሰጪ መሆኑን እንደሚያሳይም አምባሳደር ፍጹም አስታውቀዋል መረጃዉ የተገኘዉ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነዉ፡፡፡፡