7ኛዉ አለም አቀፍ የሆቴልና ቱሪዝም ኢንቨስትመንት አዉደ ርዕይ በሚሊንየም አዳራሽ ተከፈተ

ሰባተኛዉ አለም አቀፍ የሆቴልና ቱሪዝም ኢንቨስትመንት አዉደ ርዕይ ዛሬ በሚሊንየም አዳራሽ ተከፍቷል፡፡

ኢትዮጵያ እያስተናገደችው ያለው አዉደ ርዕይ ለሶስት ቀናት እንደሚቆይ ታዉቋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳዉ አዉደ ርዕዩን ሲከፍቱ እንዳሉት ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የቱሪዝም ሃብት በመጠቀምና በማስተዋወቅ ከዘርፉ ተገቢዉን ጥቅም ማግኘት እንደሚገባት ጠቁመዋል፡፡

በአዉደ ርዕዩ ላይ አለም አቀፍና ሃገራዊ ድርጅቶች ለዘርፉ የሚሆኑ ምርትና አገልግሎታቸዉን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

አዉደ ርዕዩ አለም አቀፍ የንግድ ተቋማት በአፍሪካ የሚኖራቸዉን ተሳትፎ ለማሳደግም ያለመ እንደሆነ ተነግሯል፡፡