ደረጃቸውንና ጥራታቸውን ባልጠበቁ ዕቃዎች ግዢ ሀብት እንዳይባክን እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

ደረጃቸውን እና ጥራታቸውን ያልጠበቁ እቃዎች ግዢ መንግስትን ለሀብት ብክነት እንዳይዳርጉ ለማድረግ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለ221 እቃዎች ደረጃ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መግባቱ ተገለጸ፡

የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ከኮብ እንደተናገሩት ችግሩን ለመፍታት የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ጋር በመተሰባበር ተቋማቱ በጋራ የሚጠቀሟቸውን 351 እቃዎች ላይ ጥናት በማድረግ ለ221 እቃዎችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል ደረጃ ወጥቶላቸው ተግባራዊ መሆን ጀምሯል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ የሚገዙ እቃዎች ላይ የጥራት ችግሮች የመንግስት ያለውን ውስን ሀብት ለብክነት ዳርጓል ነዉ ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ እና የመንግስት ግዢ ንብረት ኤጀንሲ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በተለይ ቋሚ የቢሮ እቃዎች እና የግንባታ እቃዎች ላይ የሚስተዋሉትን የጥራት ችግሮችን ለመቅረፍ በማሰብ ከ75 ተቋማት ለተውጣጡ የግዢ እና ንብረት አስተዳደር ባለሞያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ላይ የተገኙ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኃላፊዎች እና ባለሞያዎች ከዚህ በፊት አብዛኛው የንብረት ግዢ ደረጃውን እና ጥራቱን ያልጠበቀ በመሆኑ መስሪያ ቤታቸው ለተጨማሪ ወጪ እና ብክነት ሲዳረግ እናደነበር ገልጸዋል፡፡