ሴቶች ከሚያመርቷቸዉ ዕደ-ጥበብ ዉጤቶች በድካማቸዉ ልክ ተጠቃሚ አለመሆናቸዉ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ሴቶች በባህላዊ መንገድ ከሚያመርቷቸዉ የዕደ-ጥበብ ዉጤቶች በሚሰሩት ልክ ተጠቃሚ አለመሆናቸዉን  የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚንስቴር ገለፀ፡፡

ይህን ለመቀየር ሚኒስቴሩ ዛሬ ባዘጋጀው መድረክ ላይ የተገኙት ሚኒስትር ያለም ፀጋይ እንደተናገሩት ከዚህ በኃላ ለሴቶች የመስሪያ ቦታና ብድር እንዲያገኙ እንዲሁም የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸዉ ሁኔታዎች ይመቻቻሉ፡፡

ዘርፉ እንዲጠናከር መንግስት ትኩረት ሰቶ እንደሚሰራ ሚንስቴሯ ገልፀዋል፡፡

እንደ ሚንስትር ያለም ገለፃ ሴቶችን ለሚያሳትፈዉ የዕደ-ጥበብ ስራ ትኩረት መስጠት ለስራ ዕድል ፈጠራ፣ ለቱሪዝም ፍሰት መጨመርና የዉጭ ምንዛሬን ለማግኘት ይጠቅማል፡፡

በመድረኩ የተገኙት ተሳታፊዎችም  መንግስት ለዘርፉ የሰጠዉ ትኩረት ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዉ ከዚህ በኃላ እንዲሻሻል ጠይቀዋል፡፡

ሌሎች ሀገሮች ከዘርፉ ከኢትዮጵያ በተሻለ ደረጃ እየተጠቀሙ መሆኑም ተወስቷል፡፡