የሚተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የተያዘውን እቅድ ማሳካትና ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚቻል ተገለጸ

በተያዘው የክረምት ወራት የሚተከሉ ችግኞችን በተገቢው መልኩ በመንከባከብ የተያዘውን እቅድ ማሳካትና ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚቻል ተገለጸ፡፡

የናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ሰራተኞችና አጋሮቻቸው በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ስሙ ታጀብ ተራራ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ችግኞችን ተክለዋል፡፡

አስተያየታቸውን ለዋልታ የሰጡ የችግኝ ተካላ ተሣታፊዎች ችግኞችን ከመትከል ባለፈ ሁሉም አካላት በባለቤትነት ስሜት ሊንከባከብ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በየአካባቢው ችግኞችን ቢተከል የተያዘውን ዕቅድ ማሳካትና ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚቻል ጠቁመው፣ በሀገሪቱ የአፈርና ውሃ ሀብትን እንዲሁም ለመንከባከብና ጠብቆ ለማቆየት የችግኝ ተካላ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተራቆተውን የደን ሀብት ለመመለስ መሰል መረኃግብሮች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸውም አንስተዋል፡፡