የኢትዮጵያ የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት መጠን 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የገንዘብ ክምችቱ የሦስት ወራት የኢትዮጵያን የገቢ ንግድ ለማከናወን የሚያስችል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ተናግረዋል፡፡

ማክሮ ኢኮኖሚው በመዛባቱ ምክንያት ቀውስ ውስጥ ሊከት የሚችል ደረጃ ተደርሶ እንነበር የጠቆሙት ዶክተር እዮብ፤ አሁን ግን የተለዩትን ችግሮች ማስተካከል በመቻሉ ከችግሩ እተየወጣ ነው ብለዋል።

ይህም ለመጠባበቂያ ገንዘቡ መገኘት ምክንያት እንደሆነ ነው ያስረዱት፡፡

የሀገር ውስጥ ምርታማነትን በመጨመር የውጭ ምንዛሬ ግኝቱን ማሳደግ ካልተቻለ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት የሚያመጣቸው ችግሮች ፈታኝ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ችግሩን ለማስተካከል ለግሉ ሴክተር ተሳትፎ ልዩ ትኩረት መሰጠቱንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡