የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሰራተኞች ከ22 ሺህ በላይ ችግኞች ተከሉ

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች በቂሊንጦና ቦሌ ለሜ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ22 ሺህ በላይ ችግኞችን ተክለዋል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከኢንዱስትሪዎች የሚለቀቀዉን የተበከለ አየር መጠን ለመቀነስ ችግኞች ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው ሚኒስቴሩ ጠቅሷል፡፡    

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር በቀጣይ ሚኒስቴሩ ይህን ተግባር አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ገልፀዋል፡፡  

ኢትዮጵያ ከአረንጓዴ ልማት ተጠቃሚ እንድትሆንና የተሻለች ሃገር ለትዉልድ ለማስተላለፍ ሁሉም ዜጋ ድርሻዉን ሊወጣ እንደሚገባና ችግኞችን ከመትከል ባለፈ መንከባከብም እንደሚገባ በችግኝ ተከላዉ የተሳተፉት የሚኒስቴሩ ሰራተኞች አሰተያየታቸዉን ለዋልታ ሰጥተዋል፡፡

በችግኝ ተከላው ከ4 ሺህ በላይ የተቋሙ ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡