የገቢዎች ሚኒስቴ በበጀት ዓመቱ 248.3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታወቀ

የገቢዎች ሚኒስቴር በ2012 በጀት ዓመት 248.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ በዘንድሮው የበጀት ዓመት ከሰበሰበው በ50 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ብልጫ ያለው ገቢ በ2012ቱ በጀት ዓመት ለመሰብሰብ አቅዷል።

በ2012 በጀት ዓመት ለመሰብሰብ ከታቀደው 248.3 ቢሊዮን ብር ውስጥ 150.1 ቢሊዮን ብር ከሀገር ውስጥ፤ 98.2 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከጉምሩክ ለመሰብሰብ መታቀዱን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሚኒስቴሩ የ2011 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2012 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ሲቀርብ እንደተገለፀው፤ በበጀት ዓመቱ ሊሰበሰብ የታቀደው ብር ከ2011 ጋር ሲነፃፀር የ50.1 ቢሊዮን ብር ብልጫ ይኖረዋል ብሏል፡፡

 

ከሀገር ውስጥ ለመሰብሰብ ከታቀደው ገቢ 92 በመቶ ያህሉ ከቀጥታ ታክሶች እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በጉምሩክ ደግሞ 67 በመቶ ያህሉን ገቢ ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ኤክሳይስ ታክስ ለመሰብሰብ ታቅዷል ነው የተባለው፡፡

በሀገር ውስጥ ከሚሰበሰበው ውስጥ 150.1 ቢሊዮን ብር ውስጥ 68 በመቶውን የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እንዲሰበስብ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሰጠው የገቢ ዕቅድ በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ከታቀደው ገቢ ውስጥ 41 በመቶውን (101.6 ቢሊዮን ብር) የሚሆነውን ይሸፍናል፡፡

በጉምክ በኩል ይሰበሰባል ተብሎ ከሚጠበቀው 98.2 ቢሊዮን ብር ውስጥ ደግሞ ሞጆ እና ቃሊቲ ጉምሩክ ቅርንጫፎች 72 ቢሊዮን ብር ወይም የጉምሩክን ዕቅድ 73 በመቶ ድርሻ ይይዛሉ ተብሏል፡፡

ሌሎችም የገቢዎችና የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በየደረጃቸው የሚሰበስቡት ገቢ መጠን ተዘርዝሮ በዕቅዱ መቅረቡን

የገቢዎች ሚኒስቴር