ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚደረገው የሰራተኞች የሥራ ስምሪት በይፋ ተጀመረ

መርሃ ግብሩን የኢትዮጵያ መንግስትን በመወከል የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በመወከል ደግሞ በኢትዮጵያ የሳዑዲ አምባሳደር ሳኒ ጀማል አብደላ አስጀምረዋል፡፡

ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ  ቀደም ሲል የነበራቸውን የቆየ ግንኙነት ለማጠናከር በበርካታ ዘርፎች እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ  ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚያቀኑ ዜጎችም የሀገራቸው አምባሳደር በመሆን ለሄዱበት ዓለማ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሰራተኞቹ የሀገሪቱን ህግ በማክበር እንዲንቀሳቀሱና በህገወጥ ደላሎች የማማለያ ቃላት እንዳይሸነገሉም አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሳዑዲ አምባሳደር ሳኒ ጀማል በበኩላቸው የሥራ ስምሪቱ ተቋርጦ የነበረው ስምሪቱ ህጋዊና ሙያዊ በሆነ ሁኔታ እንዲቀጥል በማሰብ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ባለሙሙዎች ሀገራቸው እንደምትፈልግና  ስምሪትም እንደምትጀምር መግለፃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡