የአሲዳማ አፈርን ለማከም የሚያስችል ኖራ እንዲቀርብላቸው አርሶአደሮች ጠየቁ

በኢትዮጵያ አሲዳማ አፈር ከሚገኝባቸው አንዱ በሆነው የስልጤ ዞን የአሲዳማ አፈር ለማከም የሚያስችለውን የኖራ እጥረት እንዲቃለልላቸው የዞኑ አርሶአደሮቹ ጠየቁ፡፡

የአሲዳማ አፈርን ለማከም የሚያስችላቸው የኖራ አቅርቦት በሚፈልጉት ደረጃ አለማግኘቱ በምርታቸው ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩን ለዋልታ አስተያየታቸውን የሰጡ አርሶአደሮች ተናግረዋል፡፡

የዞኑ አስተዳደር በበኩሉ በዞኑ የኖራ እጥረት ከመኖሩም ባሻገር ለማጓጓዝ የሚፈለገው እንቅስቃሴ ወጪውን በእጥፍ እያናረ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም ከክልሉ መንግስት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ክልሉ ግብርና ቢሮ በበኩሉ ከክልሉ አፈር 43 በመቶ አሲዳማ በመሆኑ ኖራ የሚገኝባቸውን አካባቢዎችን በጥናት በመለየታቸው በቅርቡ ኖራውን የሚፈጩ ወፍጮች ይተከላሉ ብለዋል፡፡

የኖራውን እጥረት ለመፍታት ሌሎች አማራጮችንም በመጠቀም እንደሚሰሩም ጭምር ነው ያስታወቀው፡፡

የግብርና ሚኒስቴርም እንዲሁ ለመፍትሔው ከክሉ ጋር በጋራ እሰራለው ብለዋል፡፡