የድሬዳዋ ከተማ የ2012 በጀት ከ2 ቢሊየን 834 ሚሊየን ብር በላይ ሆኖ ፀደቀ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማዋን የ2012 በጀት 2 ቢሊየን 834 ሚሊየን 440 ሺህ ብር አድርጎ አፀደቀ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን 2ኛ የስራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ በትናንትናው ዕለት አጠናቋል፡፡

መደበኛ ጉባኤው በአስተዳደሩ የ2011 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ማድረጉ ነው የተነገረው፡፡

በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይም ምክር ቤቱ ለሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ሃላፊነት በእጩነት የቀረቡት የወይዘሮ ከሪማ አሊን ሹመት አፅድቋል፡፡