የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ መሠረት ማስፋት የሚያስችል የሦስት ዓመት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ መሠረት ማስፋት የሚያስችል ለሶስት ዓመታት የሚተገበር በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ (ዩኤስ ኤይድ) የሚደገፍ እና በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት የሚመራ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የኢኮኖሚ ሪፎርም ይደግፋል ሲሉ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱን ለማስፈፀምም መንግስት በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ታግዞ እንደሚሰራ የገለፁት ገዢው፤ በኢንቨስትመንት ማስፋፊያ፣ በስራ አጥነት ቅነሳ እና ጥናትን መሠረት ባደረጉ ፕሮጀክቶች ላይ ይሰራልም ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ በተጀመረው የኢኮኖሚ ሪፎርም የፖሊሲ ምክረ ሐሳብ በማፍለቅ በኩል እገዛ እንደሚያደርግ የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የወሰደችውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ የአሜሪካ መንግስት እንደሚደግፍ የገለፁት በኢትዮጵያ የዐሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር ለማሻሻያው ተግባራዊነት እና ተፈፃሚነት መንግስታቸው ያላሰለሰ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ ላላፉት ሦስት ዓመታት በትምህርት፣ በጤና እና በኃይል ልማት ዘርፎች ከሦስት ቢሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስት ማድረጓንም አምባሳደሩ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱን  ዩኤ ኤይድ በገንዘብ የሚደግፈው መሆኑም ተገልጿል።