የጃፓን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ቢሰማሩ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አስታወቀ

የጃፓን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ቢሰማሩ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አስታወቀ።

በደቡብ ኮሪያው እና በጃፓኑ የስራ ጉብኝት የተሳተፉት የሚኒስትሮች ልዑካን ከ7ኛው የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት መድረክ ጎን ለጎን ከጃፖኑ ማሪቦኒ ድርጅት ጋር የቢዝነስ ውይይቶችን አካሂደዋል።

በውይይቱ የማሪቦኒ ድርጅት በኢትዮጵያ መሰማራት በሚፈልግባቸው ዘርፎች ዙሪያ ገለፃ የተደረገ ሲሆን፣ በሀገሪቱ በኢነርጂ፣ በማዕድንና በቡና ምርት ላይ እሴት በመጨመር ላይ ፍላጎት እንዳለው የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ማሳሜ ካሱካኪ አስረድተዋል።

ከኢትዮያ በኩል በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት የውጭ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት የሚያስችሉ የማሻሻያ እና የአሰራር ማስተካከያ መደረጉ ተመልክቷል።

ባለሀብቶች በማዕድን፣ በኢነርጂ፣ በኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኪራይ እንዲሁም፣ በቡና ዘርፍ ቢሰማሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ በማስረዳት በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

መንግስት ለባለሀብቶቹ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ማበረታቻ እንደሚሰጥም ልኡካኑ ለባለሃብቶቹ ገልጸውላቸዋል።