ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የቶሺባ ኩባንያን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐብይ አህመድ የቶሺባ ኩባንያን ጎብኝተዋል፡፡

ኩባንያው በዋናነት የኤሌክትሮኒክስ አምራች ሲሆን ፤በሀይልና በማህበራዊ መሰረተ ልማት ዘርፎች ላይ በመስራት ላይ ነው፡፡

ቶሺባ እ.አ.አ በ1939 ሲመሰረት በ1978 ደግሞ መጠሪያውን ወደ ቶሺባ ኮርፖሬሽን ቀይሯል፡፡

ኮርፖሬሽኑ  በርካታ ንዑስ ኩባንያዎችን ያቀፈ ሲሆን  የተለያዩ ምርቶች ላይ የተሰማሩ አራት  ግዙፍ ፋብሪካዎች አሉት፡፡

 ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር  ዐብይ የተጎበኘው በሃይል ዘርፍ ስር ያለው የቴክኖሎጂ አምራች ኩባንያው ነው።

የኢፌዴሪ መንግስት ለቴክኖሎጂ ዘርፍ ቅድሚያ ሰጥቶ እየስራ እንደሚገኝ ያነሱት  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ  ኩባንያው በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋዩን እንዲያፈስ ጠይቀዋል።

የቶሺባ ኩባንያ እ.አ.አ በ2017 ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል፡፡