አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለሚያቃልሉ አዳዲስ ሐሳቦች ትኩረት እንደሚሰጥ ገለፀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር በከተማዋ የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ማቃለልና መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ እና የኑሮ ውድነቱን የሚቀርፉ አዳዲስ ሀሳቦች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።

በአቅራቢ እና ተጠቃሚ መሃል ያሉ ህገ ወጥ ደላላዎችን ሙሉ በሙሉ በማውጣት ሸማች እና አቅራቢ በቀጥታ የሚገናኝባቸው መንገዶችንም የከተማ አስተዳደሩ እየዘረጋ እንደሆነ ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡