በጉምሩክ ኮሚሽን የጂግጂጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የህግ ማሰከበር የሥራ ኃላፊዎች  በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጉምሩክ ኮሚሽን የጂግጂጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የህግ ማሰከበር የሥራ ኃላፊዎች በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የጂግጂጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የህግ ማሰከበር ኃላፊ አቶ አህመድ መሐመድ እና ምክትል ኃላፊያቸው አቶ አብዱልዋህድ አብዱላህ ናቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡

ግለሰቦቹ ከህገ ወጥ የኮንትሮባንድ ዝውውር ጋር በተያያዘበከባድ የሙስና ወንጀል በመጠርጠራቸው በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡