የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያን የቡና ምርት ለማሳደግ የሚያስችል የ15 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጄክት ይፋ አደረገ

የአውሮፓ ሕብረቱ ካፌ ፕሮጄክት የኢትዮጵያን የቡና ምርት ለማሳደግ የሚያስችል የ15 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጄክት ይፋ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳኒ ረዲ ፕሮጄክቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቡና አምራች ሀገር ብትሆንም፣ ከዘርፉ የሚገኘው ጥቅም ከምርቱ አንፃር ዝቅተኛ በመሆኑ ፕሮጄክቱ ይህን ችግር በመቅረፍ ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡
የካፌ ፕሮጄክት አስተባባሪ አቶ ፍቅሩ አመኑ በበኩላቸው ፕሮጄክቱ በቡና ምርት ላይ የሚደረገውን የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል፡፡

ፕሮጄክቱ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በአማራ፣ ደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም ኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ 28 ቡና አምራች ወረዳዎች ተግባራዊ ይሆናል፡፡