የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

ከልማት አጋሮችና ከዲፕሎማሲያዊ ማህበረሰብ ጋር በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከልማት አጋሮችና ከዲፕሎማሲያዊ ማህበረሰብ ጋር በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የውይይት መድረክን በንግግር ከፍተዋል፡፡

ኢኮኖሚያዊ ገጽታውን ለመለወጥ የተሰሩትን ቁልፍ ክንውኖች ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያን በ2030 የአፍሪካ ብልጽግና ምልክት እንድትሆን የሚያስችለውን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡  

ይህንኑም ለማሳካት የልማት አጋሮች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡