ኤጀንሲው ፈቃድ ወይም የእውቅና ፈቃድ እድሳት ሪፖርት ባልወጣለት የትምህርት ተቋም ቀድሞ መመዝገብ እንደማይቻል ገለፀ

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የ201 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የእውቅና ፈቃድ ሙሉ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

መረጃው በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመዝግበው መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የሚያገለግል መሆኑንም ነው ኤጀንሲው የገለፀው፡፡

ወቅታዊ መረጃው እስከ 2011 ዓ.ም መጨረሻ ያለውን የሚያካትት ሲሆን በሂደት ላይ ያሉትን ተከታትሎ እንደሚያሳውቅም ገልጿል፡፡

ይደርሳል በሚል የእውቅና ፈቃድ ወይም የእውቅና ፈቃድ እድሳት ሪፖርት ባልወጣለት የትምህርት ተቋም ቀድሞ መመዝገብ ክልክል እንደሆነም ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው፡፡