የ2012 የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል 

የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ በነገው ዕለት ይፋ እንደሚደረግ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በ2011 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ማለትም /የ12ኛ ክፍል ፈተና / ለመውሰድ ከተመዘገቡት 322 ሺህ 717 ተማሪዎች መካከል 319 ሺህ 264 የሚሆኑት ፈተናውን ወስደዋል፡፡

የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች መግቢያ የሚወሰነው በአራት መሰረታዊ የትምህርት አይነቶች ውጤት መሠረት አድርጎ እንደሆነ መገለፁ ይታወሳል፡፡

ይህ የሆነውም የተጋነነ የፈተና ውጤት በመታየቱ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴርና የክልል የትምህርት ቢሮ ከቀናት በፊት በጋራ በሰጡት መግለጫ  መናገራቸውም አይዘነጋም፡፡