27 ሚሊዮን ብር የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ ወደ አገር ውስጥ ሊገባ ሲል ተያዘ

የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በቦሌ አለም አቀፍ አየርመንገድ በኩል ወደ አገር ሊገባ የነበረ 27 ሚሊዮን ብር የሚገመት 10 ነጥብ 8 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

የጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ስር ያዋሉት ሄሮይን እና ኮኬን የተባሉ አደንዛዥ እፆችን ነው፡፡

አደንዛዥ እፆቹን አንድ ናይጄሪያዊ ዜጋ በያዘው ቀላል ሻንጣ ውስጥ ደብቆ ለማለፍ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ተገኔ ደረሰ በተለይ ለኢቢሲ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል እየሰራው ባለው ስራ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች በመያዝ ላይ ይገኛሉ።