በ1.4 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚገነባው የአባይ ወንዝ ተለዋጭ ድልድይ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

በባህር ዳር ከተማ የአባይ ወንዝ ላይ ተለዋጭ ድልድይ 1 ቢለዮን 400 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ ለመገንባት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

ድልድዩ 380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር ስፋት እንደሚኖረውና ወጪውም በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ተናግረዋል።

የድልድዩ ግንባታ 3 ዓመታት እንደሚፈጅ እና ስራው የሚከናወነው በቻይናው ሲሲሲሲ ተቋራጭ ድርጅት መሆኑም ተገልጿል።

አንድ ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚጠይቀው የድልድዩ ግንባታ ዛሬ ይጀመራል።

የባህር ዳር ጭስ አባይ የ22 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ ትናንት መጀመሩ በወቅቱ ተገልጿል።(ምንጭ፡-ኢዜአ)